News Detail

National News
Oct 23, 2020 686 views

የትምህርት ሚኒስትሩ በአለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በአለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ በቨርችዋል እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ጉባኤውን የጋና፣ የኖርዌይ፣የእንግሊዝ መንግስት እና ዩኔስኮ በ ጋራ አዘጋጅተውታል።

ጉባኤው ስለ ትምህርት ፋይናንስ፣በኮቪድ 19 ምክንያት የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ስለመክፈት፣ የአካቶ ትምህርት ፣የማመር ማስተማር ሂደትና እና በዲጅታል ትምህርት ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ነው።

በጉባኤው ላይ በ2021 የአለም የትምህርት የትኩረት መስክ ምን መምሰል እንዳለበት የቀጣይ አቅጣጫና ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ይጠበቃል፡፡

በጉባኤው ላይ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ የትምህርት ሚኒስትሮች እና አለም አቀፍ ፖሊሲ አውጪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Recent News
Follow Us