የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ያጋጠማቸውን ችግሮች በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በነበረው የትምህርት ሥርዓት ችግር መሠረታዊ የሞራል ውድቀት አጋጥሟል፤
ይህንንም ለማስተካከል በትምህርት ዘርፉ በአጠቃላይ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት የተለያዩ ሪፎርሞች ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን አንስተዋል።
እነዚህ የተጀመሩ የሪፎርም ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ መምህራን ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ለዚህም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ጥራትና ብቃት ያላቸው መምህራንን በማፍራት ረገድ ተልኳቸውን እንዲወጡ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ድርሻ የላቀ መሆኑን አንስተዋል።
በመምህራን ስልጠና ረገድ ሃገራችን ረዘም ያለ ታሪክ ያላት መሆኗን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ አሁን ባለው ሁኔታ በሚያስተምሩበት የትምህርት ደረጃ በቂ ችሎታ ያላቸው መምህራንን በማፍራት ረገድ ተግዳሮቶች ገጥመዋል ብለዋል።
በዚህም ከመምህራን ስልጠና እና አስተዳደር ጋር የተያያዙ ችግሮችን በሚገባ ለይቶ መፍታት ካልተቻለ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እንደማይቻል ጠቅሰው ይህንን ለመፍታት ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የጥራት ኦዲት መሪ ሥራ አስፈፃማ ወ/ሮ ትዕግስት ሃ/ስላሴ በበኩላቸው የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ሥራቸውን በሚገባ እንዲሰሩ ወደ ብቃት ማረጋገጫ ምዝገባና እውቅና ሥርዓት እንዲገቡ ማድረግ ይገባል ያሉ ሲሆን፤
በቀጣይ ኮሌጆቹ ምዝገባ በማድረግ የብቃት ማረጋገጫ እውቅና ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱበት ሥርዓት ተግባራዊ ይደረጋልም ብለዋል።
በመድረኩም ኮሌጆቹ ጥራትና ብቃት ያላቸው መምህራንን በማፍራት ረገድ ተልዕኳቸውን እንዲወጡ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆኑ ሁሉም ባለድርሻ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
በምክክር መድረኩ የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ የመምህራን ኮሌጅ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።