News Detail

National News
Jul 31, 2025 52 views

ትምህርት ለሀገር እድገት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ያበረክት ዘንድ የዘርፍ ባለሙያዎች ጥሩ ሥነ-ምግባር የተላበሱ፣ የተቋሙን ተልዕኮ በሚገባ የሚፈጽሙና የሚያስፈጽሙ ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳሰቡ።

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በሚኒስቴሩ እና በሀገራችን የ2017 እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም የልማት ዕቅድ እንዲሁም በተቋሙ እየተካሄዱ ባሉ የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂደዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ትምህርት ለሁለንተናዊ እድገት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ያበረክት ዘንድ የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ጥሩ ሥነ-ምግባር የተላበሱ፣ዘመናዊና የተቋሙን ተልዕኮ በሚገባ የሚፈጽሙ አርኣያነት ያላቸው ሠራተኞች ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ በቅንነትና በብቃት እንዲወጡ ምቹ የሥራ አካባቢ መኖር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም ለማሳካት በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በውይይት መድረኩ የሀገሪቱን የ2018 ዓ.ም የልማት እቅድ ባቀረቡበት ወቅት የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች የሀገርና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለተጀመሩ ተስፋ ሰጪ የለውጥና ዓበይት ሥራዎች ውጤታማነት ሃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አንስተዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው በ2017 ዓ.ም ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸውን ሥራዎች አስጠብቆ ማስቀጠልና ዝቅተኛ ውጤት የተመዘገበባቸው ሥራዎችን በልዩ ሁኔታ በመያዝ በቀጣይ በጀት ዓመት በትኩረት እንደሚገባ አጽናኦት ሰጥተዋል፡፡
የሚኒስቴሩ ሰራተኞችም በቀረቡ ሰነዶች ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አንስተው በከፍተኛ አመራሮቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
Recent News
Follow Us