News Detail
Jan 31, 2026
24 views
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ኢንዲስትሪ ትስስር ጥራትና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እንደሚያስችል ተጠቆመ፤
ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር አተኩረው እንዲሰሩ እየተሰራ ይገኛል።
የከፍተኛ ትምህርት የምርምና የማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሠራዊት ሐንዲሶ (ዶ/ር) እንደገለጹት የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ጥራትና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጻኦ ይኖረዋል።
የትምህርት ምርምርና ስልጠና ተቋማት ጥራት መሻሻል የኢንዲስትሪዎችን ምርታማነትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነተ እንደሚያሳድገውም ዶክተር ሠራዊት ገልጸዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ዋነኛ አቅሞች በመሆናቸው ተጽዕኗቸውን በተጨባጭ ወደተለወጠ የኢኮኖሚና እድገት ማሸጋገር እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለኢኮኖሚና ለማህበረሰባዊ ለውጥ እኩል አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ በመሆኑ በተደራሽነትና በተሳትፎ የመቀየራቸውን ያህል ጥራት ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰለጠነ የሰው ሀይል በማፍራት ለኢንዲስትሪውና ለሀገር እድገት የድርሻቸውን አበርክተዋል ብለዋል።
አክለውም በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን በማስጠበው ከኢንዱስትሪው ጋር ጠንካራ ትስስርና የትብብር እንዲፈጥሩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ለማጠናከር የወጣውን አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም በወጡ መመሪያዎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ መሆኑን ዶክተር እዮብ አብራርተዋል።