News Detail
Jul 24, 2025
170 views
የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅርቦት ለማሻሻል አማራጭ የመምህራን ትምህርት ፕሮግራም በመጪው የትምህርት ዘመን እንደሚተገበር ተገለጸ።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅርቦት ለማሻሻል በ2018 ዓ.ም አማራጭ የመምህራን ትምህርት ፕሮግራም በ6 ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ ይደረጋል።
የመርሃ ግብሩ ዓላማ የመምህራንን አጠቃላይ አቅርቦት በማሻሻል ረገድ የሚስተዋሉ እጥረቶችና የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት መሆኑንም ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።
በአማራጭ የመምህራን የትምህርት መርሃ ግብሩ ከምሁራን ጋር የተመከረበት ፣ በየደረጃው የሚገኙ መምህራንና ሌሎችም የዘርፉ ባለድርሻዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉበትና በውይይት ከዳበረ በኋላ መጽደቁን አብራርተዋል።
አማራጭ የመምህራን ትምህርት መርሃ ግብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲተገበር ከአሁን በፊት በትምህርት ዙሪያ በትኩረት እንዲሰሩ በተለዩ 6 ዩኒቨርስቲዎችና ክልሎች መላኩን ጠቁመዋል።
ከሁለተኛ ደረጃ መምህራን አቅርቦት ባሻገርም በቅድመ አንደኛ ደረጃ ላይ ያለውን የመምህራን አቅርቦት ለማሻሻል ፕሮግራሙ እንደ አንድ አማራጭ እንዲወሰድ ፍሬም ዎርኩ ለክልሎች እንዲደርስ መደረጉንም ክብርት ወ/ሮ አየለች ጨምረው ተናግረዋል።
የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው አማራጭ የመምህራን ትምህርት ፕሮግራሙ የመምህራንን አቅርቦት ለማሳደግ የሚያስችል አማራጭ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፕሮግራሙ በመጪው የትምህርት ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ በትምህርት ላይ በሚሰሩ 6ቱ ዩኒቨርስቲዎች የሚተገበር ቢሆንም ውጤቱ እየታየ እየተሻሻለና እየዳበረ እንደሚሄድም ሃላፊው አክለው ገልጸዋል።
Recent News
Jul 11, 2025