News Detail
Nov 11, 2025
21 views
ትውልድን የመገንባት መንገዳችን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ስለሆነ ዘርፉን የሚያሻግሩ አማራጮችን ማስፋት እንደሚገባ አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ አሳሰቡ፤
ትውልድን የመገንባት መንገዳችን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ስለሆነ ዘርፉን የሚያሻግሩ አማራጮችን ማስፋት እንደሚገባ አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ አሳስበዋል።
በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ የለውጥ ተግባራት ተነድፈው እየተተገበሩ መሆኑት የገለጹት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ባለፈው የትምህርት ዘመን ጸድቆ ወደትግብራ የገባውን የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ በሚገባ መተግበር ይገባል ብለዋል።
አያይዘውም ለተማሪዎች ውጤታማነት የትምህርት ቤት ምገባ፣ የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በትኩረት እየተሰሩ መሆኑን አንስተው በዚህ ዓመትም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሰገንዝበዋል።
በተጨማሪም የመምህራን የጥቅማጥቅምና መሠል ጥያቄዎችን ለመመለስ የክልልና ከተማ መስተዳድሮች የእቅዳቸው አካል አርጎ ከመስራት ባለፈ በአካባቢ ያለን ሀብት አሟጦ በመጠቀም ለሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መልስ መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በመጨረሻም በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ለተቀመጡ ቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም የክልልና የከተማ መስተዳድር ት/ቢሮዎች ተጠያቂነትን በማረጋገጥ በሀላፊነት መንፈስ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።