News Detail

National News
Oct 24, 2020 686 views

የትምህርት ቤት አመራሮችን አቅም ለማሳደግ የስልጠና ማንዋል ተዘጋጅቷል:-ትምህርት ሚኒስቴር

ለትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች የስልጠና ሂደት ለማሻሻል የሚያስችሉ የ ማሰልጠኛ ማንዋሎች መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ( ፒ ኤች ዲ) ገረመው ሁሉቃ የትምህርት አመራሩን አቅም በማሳደግ በትምህርት ቤቶች ውጤት ለማስመዝገብ በሚያስችል መልኩ ሪፎርሞቹ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

የስልጠናው ለውጡም ከ ንድፈ ሀሳብ በዘለለ በተግባር አመራሮቹ ትምህርት ቤታቸውን እና አካባቢያቸውን መሰረት በማድረግ የሚሰለጥኑበት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተነግሯል፡፡

የተዘጋጁ ሞጁሎች የትምህርት ቤት አመራሮች እየሰሩ የሚማሩበት እየተማሩ የሚሰለጥኑበት በመሆኑ የትምህርት አመራሩን ሙያዊ ብቃት፣ተወዳደሪነት እና ተነሳሽነት የሚጨምሩ መሆናቸውን ሚኒስቴር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

አዲስ የተዘጋጁት የስልጠና ማንዋሎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣የመምህራን ኮሌጆች ፣የክልል ትምህርት ቢሮዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር በተውጣጡ ባለሙያዎች እየተገመገሙ እና የማጠናከሪያ ሀሳቦች እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡

የስልጠና ማንዋሉ በዚህ ዓመት በተመረጡ አምስት ክልሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ከተደረጉ በኋላ በመላ ሀገሪቱ የሚተገበር መሆኑም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

Recent News
Follow Us