News Detail
Oct 24, 2020
910 views
ኢትዮጵያ ለትምህርት ዘርፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዓለም አቀፉ የትምህርት ጉባዔ መድረክ ላይ ነው።
ከትናንት በስተያ የተጀመረው ጉባዔው ዛሬም የቀጠለ ሲሆን ከትምህርት ቤቶች መልሶ መከፈት ጋር በተያያዘ የትምህርት ጥራትንና አካታችነትን በቀጣይ ለማረጋገጥ አገራት ቁርጠኝነታቸውን የሚገልፁበትና ቃል የሚገቡበት ነው፡፡
በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያን በመወከል እየተሳተፉ የሚገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) መንግስት ለትምህርት ዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ትኩረትና ቁርጠኝነት አብራርተዋል፡፡
በዓለም አቀፉ የትምህርት ጉባዔ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች፣ የ13 አገራት መሪዎች፣ የ13 ዓለም አቀፍ ድርጅት መሪዎች እና ከሁሉም ክፍለ አህጉራት የተመረጡ የትምህርት ሚኒስትሮች እየተሳተፉ ነው።