News Detail
Oct 23, 2020
533 views
ኢትዮጵያ እና ሩስያ በትምህርት ዘርፍ የሚያደርጉትን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌት ተረኪን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የጋራ ኮሚሽን ጉዳይ እና በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የሁለቱ ሀገራት የጋራ ኮሚሽን በሚካሄድበት ሁኔታና ስለሚከናወኑ ተግባራት ምክክር አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም በሩስያ መንግስት በሚሰጡ የነፃ ትምህርት እድሎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቭጌት ተረኪን ሩስያ ለትምህርት ዘርፉ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ተናግረዋል፡፡