News Detail

National News
May 09, 2024 976 views

የጃፓኑ ቶፓን ግራቪቲ የሕትመት ፋብሪካ በኢትዮጵያ የማምረት ሥራ ሊጀምር ነው ።

የጃፓኑ የሕትመት ፋብሪካ ቶፓን ግራቪቲ በኢትዮጵያ የማምረት ሥራ ሊጀምር መሆኑ ተገልጿል፡፡
ኩባንያው በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሚገነባው ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ በርካታ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።
ቶፓን ግራቪቲ የህትመት ፋብሪካ በኢትዮጵያ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የመማሪያ መጽሐፍትን በማተም በትምህርት ዘርፉ ላይ እያጋጠመ ያለውን የመጽሐፍ እጥረት ለመቅረፍ ይሰራልም ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ ፋብሪካው ዓለም አቀፍ የደህንነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ሚስጢራዊ ሕትመቶችን ለማተም እንደሚያስችልም ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከዚህ ቀደም በጃፓን፣ ቶኪዮ በሚገኘው ‘Toppan Gravity ‘ዋና መስሪያ ቤት የስራ ጉብኝት በማድረግ ከተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር የህትመት ሥራን በኢትዮጵያ መጀመር በሚቻልበት ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።
Recent News
Follow Us