News Detail
ተማሪዎችን መሰረት ያደረገ ፆታዊ ጥቃት መከላከል የሚያስችል መመሪያ በመሻሻል ላይ ነው፡፡
የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክተር ወ/ሮ የሺሃረግ ነጋሽ ከዚህ በፊት በሥራ ላይ የነበረው መመሪያ ውጤታማ ቢሆንም በአተገባበር ዙሪያ አንድ አንድ ውስንነቶ የነበሩበት ነው ብለዋል፡፡
መመሪያውን ለመከለስ የተፈለገበትም በአገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ከዘላቂ የልማት ግቦች፣ ከስድስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር፣ ከትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ፣ ከኢትዮጵያ የትምህርት ሕግ፣ ከአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ጋር በተጣጣመ መልኩ ለማዘጋጀት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የፆታዊ ጥቃት አይነቶች፣ የሚወሰዱ የእርምጃ አይነቶች፣ የአቤቱታ አጣሪና ውሳኔ ሃሳብ አቅራቢ ኮሚቴ አወቃቀር፣ የውሳኔ ሃሳብ አቀራረብና የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓትና የቅጣት ሪኮርድ መቆያ ጊዜ በድንጋጌዎች ከተካተቱ መካከል ለአብነት የሚጠቀሱ መሆኑን ከቀረበው ሰነድ ለማወቅ ተችሏል።
በመድረኩም ፆታን መሰረት በማድረግ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መቆጣጠርና መከላከል እንዲሁም ሕጋዊ ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ የተሰራ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጓል።
በአራት የአገር ውስጥ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለሰባት አመታት ሲተገበር የቆየውን መመሪያ የማሻሻል ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ ክልሎች ወደ ራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ በመቀየር በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል ።
በውይይቱም ላይ ከፌዴራል ተቋማት፣ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024