News Detail
May 17, 2021
323 views
ዓለም አቀፉ "ትምህርት ለዘላቂ ልማት" ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ዩኔስኮ ከጀርመን የትምህርት እና ምርምር ሚኒስቴር ጋር በመሆን ያዘጋጁት "ትምህርት ለዘላቂ ልማት" አለም አቀፍ ጉባኤ በበይነ መረብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በጉባኤው ላይ የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል፣ የዩኔስኮ ዳይሬክተር ጀነራል ኦድሬ አዞሌ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሀመድን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች እና ከመላው ዓለም የተዋጣጡ ከ 2ሺ 500 በላይ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚሰሩ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ባለሙያዎች እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮ ተሳታፈውበታል፡፡
ጉባኤው ትኩረቱን በትምህርት ዘርፉ ላይ እንቅፋት የሆኑ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን እና የትምህርት ዘርፉ ዘላቂ እድገት እንዲያመጣ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
በጉባኤው ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ ( ፒ ኤች ዲ) ኢትዮጵያ ትምህርትን መሰረት በማድረግ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በትምህርት ዘርፉ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አብራርተዋል፡፡
ከትምህርት ተሳትፎ፣ ከመፀሀፍት አቅርቦት እና ትምህርትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ከማገዝ አኳያ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡
በትምህርት ዘርፉ ላይ የተስተዋሉ ተፈጥሯዊ ችግሮችን ከመዳሰስ ባለፈም ጉባኤው የትምህርት ዘርፉ ቀጣይነት እድገት እንዲያመጣ እና በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ አካላቶች ለዘላቂ ልማት አስተዋፆ እንዲያበረክቱ ያግዛል ተብሏል፡፡
ጉባኤው ቀጣይነት ያለው እድገት ለማምጣት የሚያግዘውን የ2030 ትምህርት ለዘላቂ ልማት ፕሮግራም መሰረት የሚጥል ከመሆኑም ባሻገር ለትግበራው አቅጣጫዎችን ያመላክታል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024