ማስታወቂያ
ማስታወቂያ
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017
Posted ከ3 ወር በፊት
Read more
ማስታወቂያ
የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫን ይመለከታል።
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017
Posted ከ3 ወር በፊት
Read more
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን እንደ ፈተና ማዕከል ለመረጣችሁ የ ‘NGAT’ ተፈታኞች በሙሉ
ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜ 01/ 2016 ዓ.ም ድረስ በመላው ሀገሪቱ ይሰጣል ተብሎ በእቅድ የተያዘው የ “NGAT’ ፈተና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በፈተና ጣቢያነት ለመረጣችሁ ተፈታኞች ብቻ የፈተናው ጊዜ የተለወጠ መሆኑን እያሳወቅን ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት የምናሳውቅ ሆኖ በሌሎች የፈተና ጣቢያዎች (ዩኒቨርሲቲዎች) ፈተናውን ለመውሰድ ያመለከታችሁ በሙሉ ፈተናው በተያዘው ዕቅድ መሰረት ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ከ8:00 (ከስምንት ሰዓት) ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር
Posted ከ4 ወር በፊት
Read more
የ2016 ዓ.ም የግል እና የመንግስት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት
የ2016 ዓ.ም የግል እና የመንግስት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት
ውጤት ለማየት ይህን ይጫኑ
Posted ከ4 ወር በፊት
Read more
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ
በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤
ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፤
1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።
2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል።
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
Posted ከ7 ወር በፊት
Read more