News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 11, 2025 20 views

የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጠንካራ ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትና ለሞራል ግንባታ መሰረት የሆነ ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ላይ ትኩረ አድርጎ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ፤ ‎34ኛው የትምህርት ጉባዔ በኦሮሚያ ብ/ክ/መ በአዳማ ከተማ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጉባኤውን ሲከፍቱ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጠንካራ ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትና ለየሞራል ግንባታ መሰረት የሆነ ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ላይ ትኩረ አድርጎ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
‎የተሻለ ዜጋ ለመፍጠር ጥራትና ፍትሃዊነትን የተረጋገጥ ትምህርት ከማቅረብ ባሻገር በጠንካራ ሞራል መሠረት ላይ የቆመ ዜጋ መፍጠር እንደሚገባም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጨምረው አስገንዝበዋል።
‎የተማሩ ብቃትና ችሎታ ያላቸውን ዜጎች ለማፍራት ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥልቀት ያለው እውቀት መስጠት እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
‎በትምህርቱ ዘርፍ እየተካሄዱ ያሉ የሪፎርም ስራዎች በተለይም የሞራል ልዕል ያለው ዜጋ ለመገንባት እየተካሄደ ባለው ስራ በማህበረሰቡ ዘንድ የተሻ መረዳት መፈጠሩንም ጠቁመዋል።
‎የጉባዔው አዘጋጅ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው ባለፉት አመታት በትምህርት ዘርፍ በተከናወኑ ሥራዎች ትልቅ እድገት መመዝገቡን ተናግረዋል።
‎በዘርፉ ከትምህርት የራቁ ዜጎችን ወደ ትምህርት ገበታ ከማምጣት ፣የመማሪያ ቁሳቁስ ከማሟላት፣ በቴክኖሎጂና ፈጠራ አንጻር አሁንም ተግዳሮቶች መኖራቸውን ዶክተር ቶላ አስረድተዋል።
‎34ኛው የትምህርት ጉባዔ አገራችን ማንሰራራት በጀመረችበት ዘመን የሚካሄድ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገውም የትምህርት ቢሮ ኃላፊው ጠቁመዋል።
Recent News
Follow Us