News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 11, 2025 23 views

34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀመረ፤

'ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም'' በሚል መሪ ቃል በተጀመረው ጉባዔ የ2017 የትምህርት ልማት ዘርፍ አፈጻጸም ይገመገማል።
‎ጉባዌው በ2018 የትምህርት ዘመን እቅድ ላይ ውይይት በማድረግ ለተሻለ አፈጻጸም የሚያግዙ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
‎በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ ጉባዔ የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
‎በተጨማሪም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፣የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶችና አጋሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
Recent News
Follow Us