News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 11, 2025 21 views

በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ስራዎች ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ሀገርን ለማሻገር ቁልፍ ሚና እንዳለው ተገለጸ። አስረኛው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይና ውድድር በይፋ ተከፍቷል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከሌሎች ተባባሪ ተቋማት ጋር በመሆን የሚያዘጋጀው አመታዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይና ውድድር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በደመቀ ሁኔታ ተከፍቷል።
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ልዩ ዝንባሌና ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎችና መምህራን የሚያገናኘውን አመታዊ አውደ ርዕይና ውድድር የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በይፋ ከፍተውታል።
ሚንስትር ዴኤታዋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ሀገርን ለማሻገር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና የሌሎች ተባባሪ ተቋማት ስራ ሀላፊዎች ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Recent News
Follow Us