News Detail

National News
May 31, 2021 242 views

የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማዘመን አምራች ዜጋን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማዘመን አምራች ዜጋን ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴሩ ጌታሁን መኩሪያ( ዶ/ር ኢንጂ)  ሚኒስቴሩ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን እና በቀጣይም የትምህርቱ ዘርፉ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ የመማር ማስተማር ሂደቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

በአሁን ሰዓት ትምህርትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በሚደረገው  ሂደት ውስጥ ለ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት እርከን  ትኩረት መሰጠቱን የገለፁት ሚኒስትሩ  ይህም ወጣቱ በቴክኖሎጂ በመታገዝ አምራች ዜጋ እንዲሆን ለማድረግ  መሆኑን ተናግረዋል።

የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እና  መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሀብት  እጥረት  ትልቅ ተግዳሮት እንደሆነ እና ተግዳሮቱን ለመፍታትም መንግስት እና አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ሀብት የማሰባበሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም በትምህርት ዘርፉ ውስጥ የሚኖረው የቴክኖሎጂ ትግበራ  ወደታች የሚወርድ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

Recent News
Follow Us