News Detail
የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማዘመን አምራች ዜጋን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴሩ ጌታሁን መኩሪያ( ዶ/ር ኢንጂ) ሚኒስቴሩ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን እና በቀጣይም የትምህርቱ ዘርፉ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ የመማር ማስተማር ሂደቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
በአሁን ሰዓት ትምህርትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በሚደረገው ሂደት ውስጥ ለ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት እርከን ትኩረት መሰጠቱን የገለፁት ሚኒስትሩ ይህም ወጣቱ በቴክኖሎጂ በመታገዝ አምራች ዜጋ እንዲሆን ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እና መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሀብት እጥረት ትልቅ ተግዳሮት እንደሆነ እና ተግዳሮቱን ለመፍታትም መንግስት እና አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ሀብት የማሰባበሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም በትምህርት ዘርፉ ውስጥ የሚኖረው የቴክኖሎጂ ትግበራ ወደታች የሚወርድ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024