News Detail
Aug 29, 2025
58 views
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በእስራኤል የክልል ትብብር ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋገሩ።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ የእስራኤል የክልል ትብብር ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር ጊላድ ሻድሞን (Gilad Shadmon) የተመራ የልዑካን ቡድን አባላትን ተቀብለው በሁለቱ አገራት መካከል በትምህርቱ ዘርፍ ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
በዚሁ ጊዜ ሚኒስትር ዴኤታው በአገራቱ መካከል የከፍተኛ ትምህርት ትብብር በተለይም በአካዳሚክ ፣ በምርምር በዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ከእስራኤል ዩኒቨርስቲዎች ልምድና ተሞክሮ መቅሰም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በፈጠራና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ፣ በግብርና ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፣ በማዕድንና በሌሎችም ዘርፎች ትብብር ማሳደግ እንደሚያስፈልግም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
የእስራኤል የክልል ትብብር ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር ጊላድ ሻድመን በበኩላቸው በኢትዮጵያና በእስራኤል መካከል የቆየ ወዳጅነትና ትብብር መኖሩን ጠቁመው አገራቸው በትምህርቱ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸዋል።
እስራኤል በግብርና በአካባቢ ጥበቃ በተለይም በውሃና አፈር ጥበቃና አያያዝ፣ በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራና በሌሎችም ያላትን ልምድ ማካፈል እንደምትችልም ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
Recent News
Sep 02, 2025
Aug 29, 2025
Aug 28, 2025
Aug 23, 2025