News Detail
Feb 13, 2026
9 views
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
በቅርቡ አዲስ የተመደቡ የቦርድ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ተረድተው ወደ ተግባር እንዲገቡ የሚያስችል የሥራ ትውውቅና መመሪያ ተሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች የተጣለባቸውን አገራዊ አደራ ለመወጣት የተመደቡበት ተቋም ተልዕኮና የሥራ ድርሻ በውል መረዳት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም አመራሩ የተሰጠውን የሥራ ኃላፊነት በጥልቀት አውቆና ተረድቶ መስራቱ ለተቋሙ ስኬት መሰረታዊ ፋይዳ እንዳለው አስገንዝበዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀትና የምርምር ማዕከል በመሆናቸው አመራሩ ግልጽ ራዕይ ይዞ መንቀሳቀሱ የተቋማዊ ለውጥ (Reform) ስራዎችን በብቃት ለመምራትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘው ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በመከናወን ላይ ያሉ የሪፎርምና መደበኛ ስራዎችን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።
አዳዲሶቹ አመራሮች የተሰጣቸውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ወደ ስራ ሲሰማሩ የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ ካለው ሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫ ጋር በማጣጣም መከወን እንደሚገባቸውም አቅጣጫ ተቀምጧል።
Recent News
የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
Feb 27, 2026
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
Feb 13, 2026