News Detail

National News
Dec 25, 2020 956 views

"ልጆቼን ወደ ትምህርት ቤት መልሱልኝ":- ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) የትምህርት ሚኒስትር

“ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ” ንቅናቄ በዛሬው እለት በይፋ ተጀመሯል። የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ልጆቼን ወደ ትምህርት ቤት ላኩልኝ በማለት ንቅናቄውን በይፋ አስጀምረዋል።

የንቅናቄው አላማም በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉና ከቤታቸው የቀሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በንቅናቄው ተማሪዎች እና መምህራን ቤት ለቤት በ መንቅሳቀስ በቤታቸው የቀሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ  የመቀስቀስ ስራ እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡

 የሀገር ተረካቢ የሆነውን ትውልድ ወደ ትምህርት ቤት በመላክ  የነገይቱን  ኢትዬጵያ ለመገንባት ሁሉም ሀላፊነት እንዳለበት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በንቅናቄው ላይ ሁሉም ባለድረሻ አካላት ተሳታፊ  በመሆን በቤት የቀሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ የበኩላቸውን እንዲወጡ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

“ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ” ንቅናቄም እስከ ቀጣዩ ማክሰኞ የሚቆይ ይሆናል።

Recent News
Follow Us