News Detail

National News
Dec 27, 2020 960 views

በፀጥታ ችግር ትምህርት ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች ላይ ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ ነው፦ ትምህርት ሚኒስቴር

በኮሮና ወረርሽኝ ዙሪያ ተገቢ ጥንቃቄ እየተደረገ በአብዛኛው አካባቢዎች ትምህርት ቢጀመርም በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ያልጀመሩ አካባቢዎችም ትምህርት እንዲጀምሩ እየሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፤ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም አካባቢ በሚባል ደረጃ ትምህርት ተጀምሯል።

ነገር ግን ከወቅታዊ የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልልና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ትምህርት አልተጀመረም። በመሆኑም በእነዚህ አካባቢዎች ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።

በዚህ ረገድ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በተለይ በትግራይ ክልል ትምህርት ለመጀመር ጁንታው ከተመደሰሰ በኋላ ነባራዊ ሁኔታን የሚገመግም ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ አካባቢው ልኳል። 

ሆኖም ግን ትምህርት ቤቶች በጁንታው ኃይል በመውደማቸው ምክንያት የመጠገን ሥራ ጊዜ መውሰዱ አይቀርም። በመተከል ላይም ተመሳሳይ ሥራ የሚሰራ ይሆናል።

Recent News
Follow Us