News Detail
Aug 24, 2020
757 views
በካናዳ አብዛኞቹ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ማቀዳቸውን አንድ ጥናት አመላከተ።
በ ካናዳ በተካሄደ አንድ ጥናት አብዛኛው ካናዳዊያን ቤተሰብ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ማቀዳቸውን ነገር ግን በ አካባቢው የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱ በይበልጥ ከተሰፉፉ ትምህርት እንዲቋረጥ እንደሚፈልጉ አመላክቷል።
በ ሌገር እና በካናዳ ጥናት ማህበር የተካሄደው ጥናት በአካባቢው ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት የወላጆችን ፍላጎት ምን እንደሚመስል ለማወቅ የተካሄደ ጥናት ነው።
በጥናቱም ጥያቄው ከቀረበላቸው እና ምላሽ ከሰጡት 66% ተሳታፊዋች ውሰጥ 63% የሚሆኑት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ማቀዳቸውን አሳውቀዋል።
ከዚህ ውስጥም 69% የሚሆኑት የ ቫይረሱ ስርጭት የሚጨምር ከሆነ ትምህርት እንዲቋረጥ እና የመማር ማስተማሩ ሂደት በቤት ውስጥ እንዲሆን እንደሚፈልጉም ጥናቱ አመላክቷል።
በ ኦላይን በተካሄደው በዚህ የዳሰሳ ጥናት ከ 18 አመት በላይ የሆኑ 1,510 ተማሪዋች 385 ወላጆች ተሳትፈውበታል።
በተያያዘም በጥናቱ 76% የሚሆኑ መላሾች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት ሲመለሱ የአፍ መሸፈኛ ጭንብል ያድርጉ ማለታቸውንም ጥናቱ አስታውቋል ።
በካናዳ ትምህርት ቤቶች ከተከፈቱ ሁለት ሳምንት ሆኗል።