News Detail
Aug 20, 2020
540 views
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የሸገር ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።
የትምህርት ሚኒስቴራ አመራሮች እና ሰራተኞች በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉ ፕሮጀክቶች መካከል የሸገር ፕሮጀክትን እና የ እንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጅ ) ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር በጋራ በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነቡ ያሉ የሸገር ፕሮጀክትንና እንጦጦ ፓርክን በተመለከቱበት ወቅት "በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መሪነት የተሰሩት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ግዙፍ ስራዎችን መስራት እንደሚቻል የሚያሳይ ነው" ብለዋል።
የዚህ ዓይነቱ ፕሮጀክት ሰው "ማድረግ እችላለሁ" የሚል ብሩህ ራዕይ እንዲኖረው ያደርጋል ነው ያሉት።
አዲስ አበባ ውስጥ የታየው ይህው ስራ በ45ሺህ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ እናደርጋለን ያሉት ሚኒስትሩ ትምህርት ቤቶቹ በራስ አቅምና በውስን ወጪ ንፁህና ውብ ስራዎችን መስራት እንደሚችሉ ማወቅ እንደሚገባ ገልፀዋል።
"ሁሉም ነገር የሚቻል እንደሆነ ከፕሮጀክቶቹ ተምረናል፤ የ12ኛ ክፍል
በኢትዮጵያ 3ሺህ 5መቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች መኖራቸውን የገለፁት ኢንጅነር ጌታሁን ተማሪዎች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው የሚማሩና ሙያዊ ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ ስርዓተ ትምህርት ተቀርፆ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ፈተናም በኦንላይን ማከናወን እንደሚቻል ማሳያዎች ሆነዋል እኛም ዝግጁ ነን" ሲሉ ተደምጠዋል።