News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Feb 03, 2022 1.3K views

ትምህርት ሚኒስቴር እና ብሪትሽ ካዉንስል በከፍተኛ ትምህርት የሰላም ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያሥችላቸዉን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ፒ ኤች ዲ) እና በኢትዮጵያ የብሪቲሽ ካዉንስል ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ነጻነት ደሞዝ ናቸዉ፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የፕሮጀክቱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ዶ/ር ሃላ ኑር፣ የብሪትሽ ካዉንስል ምክትል ዳይሬክተር ሰላማዊት አለማየሁን ጨምሮ ከብሪትሽ ካዉንስል፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሀላፊዎች እንዲሁም ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸዉ የሀዋሳ፣ጅማ እና ባህርዳር ዩኒቨርስቲዎች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን የረጅም ጊዜ አጋርነት ማጠናከር፣ ዩኒቨርስቲዎች ግጭትን በመከላከል እና የሰላም ግንባታ ያላቸዉን ሚና ማጎልበት እና ስርዓተ ጾታንና ከባቢያዊ ሁኔታን መሰረት ያደረጉ ሰላምን የሚመለከቱ ምርምሮች መደገፍ ላይ ያተኮረ ነው። 

በሂደት አገራዊ፣ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ደረጃ በሰላም ጉዳይ በጋራ መስራትን መነሻ ያደረገ ትብብርን የማጠናከር ዓላማ አለዉ፡፡

ስምምነቱ የዩኒቨርስቲ ለሰላም ትምህርትን በአካባቢያዊ ግጭት ወቅት መተግበር የተባለዉ ፕሮጀክት በአዉሮፓ ህብረት እናያለን ብሪትሽ ካዉንስል የገንዘብ ድጋፍ በብሪትሽ ካዉንስል በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያንና ሱዳንን ማዕከል አድርጎ ይተገበራል ተብሏል፡፡

Recent News
Follow Us