News Detail
Nov 07, 2025
51 views
በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ የልዑካን ቡድን በፊንላንድ ጥናታዊ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
ከፊላንድ መንግስት በተላከላቸው ግብዣ መሠረት በክቡር ሚኒስትሩ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በፊንላንድ ጥናታዊ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
በዚህ ጉብኝትም የትምህርት ሚኒስትሩን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወትና የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እኩኝ ኡኬሎ እየተሳተፉ ይገኛል።
የልዑካን ቡድኑ በቆይታው ከፊንላንድ የትምህርትና ባህል ሚኒስትር፣ ከፊላንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ የትምህርት ማዕከል፣ እንዲሁም ከሂልሲንኪ ዩኒቨርሲቲና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችን ጋር ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል።
በዚህ ጥናታዊና የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ወቅትም በኢትዮጵያና በፊላንድ የትምህርት ተቋማት ሊኖር ስለሚገባው ትብብር እና የፋይናንስ ድጋፍ ተጠናክሮ በሚቀጥልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።