News Detail
Nov 07, 2025
42 views
በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ ልዑካን ቡድን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳትፏል።
በትምህርት ሚኒስትሩ የተመራ የልዑካን ቡድን አባላት በሳማርካንድ፣ ኡዝቤኪስታን ሪፐብሊክ በተካሄደው 43ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳትፎ አድርጓል።
በዚህ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) 43ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት በዩኔስኮ ዘርፎች ያከናወነችውን ተግባራት አብራርተዋል።
በዚህም ከትምህርት፣ ከባሕል፣ ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከብዝሃ-ሕይወት ዘርፍ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ እየሰራቻቸው ያሉ ሥራዎችን ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡
አያይዘውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የተነደፉ ስትራቴጂዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው ይህ የዩኔስኮ ጠቅላላ ጉባኤ በትምህርት፣ በሣይንስ፣ በባህል፣ ተግባቦትና መረጃ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ፤ አባል ሀገራትን ለመደገፍ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መድረክ እንደሆነም ተጠቁሟል።
ክቡር ሚኒስትሩ ከጉባኤው ጎን ለጎንም ከተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር የሚያስችሉ ውይይቶችን አድርገዋል።