News Detail

National News
Jun 22, 2025 12 views

የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ኘሮግራሞች በአገራዊው የብቃት ስታንዳርድ ተመዝነው ጥራትና ተገቢነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ኘሮግራሞችን ጥራትና ተገቢነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጄና (ዶ/ር) ገልፀዋል ።
ከነዚህ ተግባራት መካከል የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ውጤት ተኮር (Outcome based) መርህን ተከትለው እንዲተገበሩ በትምህርትና ስልጠና ፓሊሲው ላይ በተመላከተው ድንጋጌ መሰረት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል።
የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ሥርዓተ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ በሱፍቃድ ኃ/ማሪያም በበኩላቸው ለ37 የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የውጤት ተኮር ብቃት መለኪያ (Competency) ተዘጋጅቶ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ሥራ መጀመሩን ገልፀዋል።
በዚህም ከ23 ዪኒቨርሲቲዎች፣ ከኢንዱስትሪዎች፣ ከሙያ ማህበራት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የየመስኩ ባለሙያዎች በክለሳ ሥራው ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በመድረኩም የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃንን ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት አካል የሆነው ውጤት ተኮር (Outcome based) የትምህርት ሥርዓት ስኬታማ እንዲሆን በተለይ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለየ መልኩ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንዲወጡም ተጠይቋል።
Recent News
Follow Us