News Detail

National News
Jun 13, 2025 10 views

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኝ ተማሪዎች አበረታቱ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሺንሺቾ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ እየተሠጠ የሚገኘውን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተዘዋውረው በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ምዘናና አስተዳደር ሥርዓቱን በማስተካከል ጠንክሮ በመሥራት እንጂ በሌላ መንገድ የሚገኝ ውጤት እንደሌለ ግልፅ እየሆነ መጥቷል፤
በመሆኑም ተማሪዎች ኩረጃንና ስርቆትን የሚጠየፉ መልካም ሥነ ምግባር የተላበሱ እንዲሆኑም አሳስበዋል።
አክለውም ተማሪዎች ጠንክረው በመማር በራሳቸው የሚተማመኑ ብቁና ተወዳዳሪ የነገ ሀገር ተረካቢ መሆን እንዳለባቸውም ምክር ለግሰዋል።
በተጨማሪም አመራርቹ በከንባታ ዞን በሺንሺቾ ከተማ በብራይት ቪዥን ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለህጻናት እየተሰጠ ያለውን ትምህርት ምልከታ አድርገዋል።
Recent News
Follow Us