News Detail

National News
Nov 22, 2024 235 views

በትምህርት ዘርፍ እየታዩ ያሉት ለውጦች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተጠቆመ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች የለውጡ መንግስት ባሳካቸውን የልማት ስኬቶችና በነበሩ ተግዳሮቶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። “የህልም ጉልበት ፣ ለእምርታዊ እድገት” በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይት መድረኩ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ይህ የውይይት መድረክ ለውጡ ያሳካናቸውን ስኬቶች ይዘን የነበሩብንን ተግዳሮቶች ለይተን ልዩ ርብርብ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ አየለች አክለውም እንደ ትምህርት ማህበረሰብ ሚናችንና የነበሩ ተግዳሮቶችን ለይተን በትኩረት ከሰራን በቀጣይ ለሀገራችንና ለህዝባችን ምንዳን ማምጣት እንችላለን ብለዋል። ስራዎቻችን በአጭርና በረጅም ጊዜ አቅደን ከሰራን አኩሪ ስኬቶችን ለማህበረሰባችን ማድረስ እንደሚቻል መገንዘብ ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በበኩላቸው በትምህርት ዘርፉ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ ቢሆንም እስካሁን ያልተሻገርናቸውና ትኩረት የሚሹ ስብራቶች መኖራቸውን ጠቅሰው ትምህርትን እንደሚመራ ተቋም እነዚህን ስብራቶች በአግባቡ ማሻሻል ካልቻልን ተወቃሽ እንሆናለን ብለዋል።
በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቢኒያም ኤሮ የእለቱን የመወያያ አጀንዳ ያቀረቡ ሲሆን ከሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።
Recent News
Follow Us