News Detail

National News
Nov 15, 2024 64 views

9ኛው የሳይንስና ምህድስና የመምህራንና የተማሪዎች የፈጠራ ሥራ ውድድር አውደ ርዕይ ተጠናቀቀ።

በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ የነበረው 9ኛው የሳይንስና ምህድስና ዘርፎች የመምህራና የተማሪዎች የፈጠራ ሥራ ውድድር አውደ ርዕይ በዛሬው እለት ተጠናቋል።
በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራና ትምህርት ቤት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ(ዶ/ር) የመምህራንና የተማሪዎች ሥራ ፈጠራ ውድድር አውደ ርዕይ ለየት ያለ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሀሳባቸውን ለሌሎች አካፍለው ድጋፍና ግብዓት የሚያሰባስቡበት መድረክ እንደነበር ገልጸዋል።
ዶ/ር ሙሉቀን አክለውም በዚህ አውደ ርዕይ የተሳተፉና የተወዳደሩ ተማሪዎችና መምህራን ይህ የመጨረሻቸው ግብ አለመሆኑን አውቀው እንደ ማስፈጠሪያ በመጠቀም ወደፊት በፈጠራ ሥራቸው ራሳቸውንና ሀገርን ወደ ሚጠቅሙበት ደረጃ እንዲደርሱ ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።
በሌላ በኩል በመድረኩ ተገኝቶ ልምዱን ያካፈለው ተማሪ እና ሥራ ፈጣሪ የሆነው ኢዘዲን ካሚል በበኩሉ ተማሪዎች በአውደ ርዕይ ተወዳድሮ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ የፈጠራ ሀሳባቸውን ወደ ቢዝነስና ህብረተሰቡን መቀየር ወደ ሚችሉበት አገልግሎትና ምርት መሸጋገር የሚችሉበትን ማሰብና ለዛም ጠንክሮ መስራት እንምደሚጠበቅባቸው ተናግሯል።
ተማሪ ኢዘዲን ከዚህ ቀደም በ2010 እና 2011 ዓ.ም በተካሄደው የሳይንስና ምህድስና የፈጠራ ሥራ ውድድር ላይ በተከታታይ ተሸላሚ እንደነበር ጠቅሶ በአሁኑ ወቅት በቱርክ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ አመት የሶፍት ዌር ኢንጂነሪግ ተማሪ መሆኑን ገልጿል። ከትምህርቱም ጎን ለጎን በፈጠራ ሥራው የራሱን ድርጅት በማቁቋም ከራሱ አልፎ ለሌሎች የሥራ እድል በመፍጠር የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑም ተናግሯል።
ተማሪ ኢዘዲን አክሎም በዚህ አውደ ርዕይ በቀረቡ የፈጠራ ሥራዎች መደነቁን በመግለጽ ወደፊት በርካታ ሥራ ፈጣሪ የሆኑ ወጣቶች እንደሚፈጠሩ ያለውን እምነት ገልጿል።
በፈጠራ ሥራ ውድድር አውደ ርዕይ ላይ በተለያዩ ዘርፎች ተወዳድረው ለአሸነፉ መምህራንና ተማሪዎች የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል።
ይህ 9ኛው የሳይንስና ምህድስና የመምህራንና ተማሪዎች የፈጣራ ሥራ ውድድር አውደ ርዕይ ትምህርት ሚኒስቴር ከስቴም ፓዎር፣ ስቴም ሲነርጂ፣ ጃይካ፣ ኢጁኬሽን ፎር ኢትዮጵያ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑ ይታወቃል።
Recent News
Follow Us