News Detail
Jul 18, 2024
752 views
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ጋር ውይይት አደረጉ
የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ጋር በትምህርት ዘርፉ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል። በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ከሀገራቸው የትምህርት ሚኒስቴር፣ ትምህርትን ከሚደግፉ የልማት ድርጅቶች ጋር በመተባበር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
አምባሳደሩ አክለውም የኢትዮጵያን የትምህርት ሪፎርም ለመደገፍ በተለይም በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የት/ቤቶችን መስፋፋትና እድሳት፣ የት/ቤት ምገባ ለማገዝና እና የተለያዩ የመምህራን ክህሎት ማሻሻያ ስልጠናዎች ለመስጠት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት በዩኒቨርስቲዎች መካከል በሚደረግ ትብብር፣ በነጻ ትምህርት እድል፣ በጋራ የምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024