News Detail
May 31, 2024
2K views
ለ12ኛ ክፍል የኦንላይን ተፈታኞች የመፈተኛ ፕላትፎርም የተሰጠ ማብራሪያ
ግንቦት 23/2016 ( የትምህርት ሚኒስቴር) ለ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ተፈታኞች የኦንላይን የመፈተኛ ፕላትፎርምን አጠቃቀም አስመልክቶ የተዘጋጀ መልዕክት
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የተዘጋጀውን የኦንላይን የመፈተኛ ፕላትፎርም እንዴት መጠቀምና ፈተና መፈተን እንደሚቻል ለማሳየት የተዘጋጀ የ4 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ገላጭ ቪዲዮ በዚህ ሊንክ https://www.youtube.com/watch?v=PdAu-FI-Q5M ገብታችሁ በመመልከትና ራሳችሁን ለፈተናው ዝግጁ እንድታደርጉ እያሳሰብን፣ ቪዲዮ ላይ ያለው የአጠቃቀም መመሪያም ለንባብ እንደሚመች ሆኖ ከዚህ በታች ቀርቧል።
1. በየመፈተኛ ክላስተራችሁ ተለይቶ ወደተቀመጠው መፈተኛ URL ትገባላችሁ።
2. ከገባችሁ በኋላ ከትምህርት ቤታችሁ የተሰጣችሁን መለያ ቁጥርና የሚስጥር ቁጥር User Name እና Password በማስገባት login የሚለውን መጫን።
3. ወደቀጣዩ ገጽ ስትገቡ ፓስወርድ ቀይሩ የሚል መልዕክት ይነበባል። ስለሆነም Current password የሚለው ላይ ከትምህርት ቤታችሁ የተሰጣችሁን በማስገባት New password የሚለው ላይ አዲስና የማትረሱትን 8 ካራክተሮችን የያዘ የሚስጥር ቁጥር በማስገባት ትቀይራላችሁ። ይህ አዲሱ ፓስወርድ ከዚህ በኋላ ወደዚህ ገጽ የምትገቡበት አዲስ መግቢያ ይሆናችኋል ማለት ነው።
4. አዲስ የቀየራችሁትን ፓስወርድ Save changes የሚለውን በመጫን ከጨረሳችሁ በኋላ Continue የሚለውን በመጫን ወደ ቀጣዩ ገጽ ትገባላችሁ።
• እዚህ ጋር የምትወስዱትን የፈተና አይነት ታያላችሁ። ከዚያም የፈተናው ስም ላይ click አድርጋችሁ ስትገቡ ቀጥታ ወደፈተናው ይወስዳችኋል።
5. እዚያው ገጽ ላይ Attempt Exam የሚለውን በመጫን በመፈተኛ ቦታችሁ በፈታኞቻችሁ የሚነገረውን የፈተና መለያ ቁጥር Quiz password የሚለው ላይ ታስገቡና start attempt የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቹን ወደምታገኙበት ገጽ ይመራችኋል።
በዚህ ገጽ
• በስተግራ በኩል የፈተናውን አይነት፣
• መሃል ላይ ከላይ የተፈታኞች ሙሉ መረጃ፣
• መሃል ላይ ከታች፣ ጥያቄዎችና ጥያቄውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የቀራችሁን ደቂቃ መቁጠሪያ እንዲሁም
• በቀኝ በኩል የተመልሱና ያልተመልሱ ጥያቄዎች መለያ (exam overview) ታገኛላችሁ።
6. መሃል ላይ በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ ብቻ ከሚያሳየው ቦታ ጥያቄውን በአግባቡ አንብባችሁ መልሱን ከመረጣችሁ በኋላ Next page የሚለውን በመጫን ወደቀጣይ ጥያቄ ማለፍ ትችላላችሁ።
7. አንድ ጊዜ የመረጣችሁትን መልስ መቀየር ከፈለጋችሁ ከእያንዳንዱ መልስ የተሰጠው ጥያቄ ስር የሚመጣውን Clear my choice የሚለውን click በማድረግ የመጀመሪያውን ማጥፋትና አዲሱን መልስ መምረጥ ይቻላል።
8. መልሱን ከመረጥን በኃላ ደግሞ ተመልሰን በድጋሜ ልናየው የምንፈልግ ከሆነ ከጥያቄው በስተግራ ባለው ቦክስ ያለችውን flag question የሚለውን click በማድረግ ጥያቄውን ተመልሳችሁ ለማየት ምልክት አድርጋችሁ ማለፍ ትችላላችሁ።
9. ምልክት ለማድረጋችሁም በስተቀኝ በኩል ያለው የጥያቄዎችን መመለስ አለመመለሳቸውን የሚያሳየው Exam overview ላይ ጫፉ ቀይ ምልክት ኖሮበት ታገኙታላችሁ።
እዚህ ቦታ
• መልስ የተሰጠባቸው ጥቁር ምልክት ሲኖራቸው
• መልስ ያልተሰጠባቸው ነጭ እና
• ድጋሜ አየዋለሁ በሚል flag question የተደረጉት ቀይ ምልክት ሆኖባቸው በቀላሉ እንዲለዩ ሆነው ይታያሉ።
10. ሁሉንም ጥያቄዎች ሰርታችሁ ስትጨርሱ Finish attempt የሚለውን ስትጫኑ የጥያቄዎቹን ቁጥር በመዘርዘር የሰራችሁትንና ያልሰራችሁትን ለይቶ ያሳያችኋል። የተመለሰውን: Answer saved ብሎ ሲያስቀምጥ ያልተመለሰውን: ፣Not yet answered ብሎ ከጥያቄው ፊት ያስቀምጣል።
11. እዚህ ጋር ያልመለሳችሁትን ጥያቄ ለመስራት Not yet answered ከሚለው ጽሁፍ ፊት ለፊት ያለውን ቁጥር በመጫን ወይም በስተቀኝ (exam overview) ጋር በመሄድ Not yet answered የተባለውን ጥያቄ ቁጥር በመጫን ወደጥያቄው ተመልሶ በመግባት መስራት ይቻላል።
12. ሁሉንም ጥያቄዎች ከመለሳችሁ በኋላ እዛው ገጽ ላይ በስተቀኝ በኩል exam overview የሚለው ጋር በመምጣት ከስሩ ያለውን Finish attempt የሚለውን ክሊክ በማድረግ በድጋሜ የተመለሱና ያልተመለሱ ጥያቄዎች ወደሚታዩበት ገጽ ይመራናል።
13. መጨረሳችንን እርግጠኛ ስንሆን እዚሁ ገጽ ላይ ከታች ያለውን Submit all and finish የሚለውን እንጫናለን። Confirmation የምትል box ላይ እርግጠኛ ናችሁ፣ ጨርሳችኋል የሚል ማረጋገጫ ጥያቄ ታያላችሁ። ያኔ ድጋሜ Submit all and finish የሚለውን በመጫን ታጠናቅቃላችሁ።
14. ካረጋገጣችሁና Submit all and Finish የሚለውን ከተጫናችሁ በኋላ ወደዋናው ገጽ ይመልሳችኋል። እዚህ ጋር የፈተናችሁን Status ማየት ይቻላል።
15. እዚህ ጋር ፈተናውን ስለጨረሳችሁ finished የሚል ጽሁፍና የተፈተናችሁበት ቀን እና የጨረሳችሁበት ሰዓት ተመዝግቦ ታያላችሁ።
16. አሁን ፈተናውን ስለጨረሳችሁ በቀኝ በኩል ጠርዝ ላይ ስማችሁ ያለበት ጋር click በማድረግ Logout በማድረግ ከገጹ መውጣት ይገባል።