News Detail
        
            May 27, 2024
        
        
            
            2K views
        
    
    
    
    ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር ሶስተኛውን ሽልማት አሸነፉ።
ኢትዮጵያን ወክለው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ አይሲቲ ውድድርን በቻይና ሼንዘን ከተማ በኮምፒውቲንግ ትራክ የተሳተፉት 3 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶሰተኛውን ሽልማት ከማሌዢይ፣ ሜከሲኮ እና ኬንያ ቡደን ጋር ተጋርተዋል።
ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሶስት የውድድር ትራኮች (Innovation, Network and Computing) ተካፋፍሎ የተካሄደ ሲሆን ከአርባ ምንጭና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በተገኙ ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ሶስተኛውን ሽልማት አሸንፎ ዛሬ ወደ አገሩ ተመልሷል።
የትምህርት ሚኒስቴር በተማሪዎቹ ውጤት የተስማውን ደስታ እየገለጸ፣ ወደፊትም የተማሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እድል የሚፈጥሩ ውድድሮች ላይ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ከመሰል ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።