News Detail
May 23, 2024
1.1K views
ሶስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር ለመሳተፍ ቻይና ገቡ።
የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር ለዓለም አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የተዘጋጀ አመታዊ ውድድር ነው።
ሁዋዌ በየዓመቱ የሚያካሂደው ይህ ውድድር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ጨምሮ ከመላው አለም የተውጣጡ ተማሪዎችን ያሳትፋል። ድርጅቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አገር አቀፍ ውድድር ሲያካሂድ ቆይቷል።
በውድድሩም የኢትዮጵያ ቡድን በሶስት ቡድኖች የተደራጁ ዘጠኝ ተማሪዎችን ይዞ ከዘጠኙ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ እና ሞሮኮ) ከተውጣጡ ተማሪዎች መካከል ተወዳድሮ በአንድ ቡድኑ ሶስተኛ ደረጃን አግኝቷል። ይህ ቡድን ሶስት ተማሪዎችን ይዞ በ8ኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ የፍጻሜ ውድድር አገሩን ወክሎ ለመሳተፍ ቻይና ገብቷል። ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም በቻይና ሼንዘን ከተማ ይካሄዳል።
ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ከግንቦት 16 እስከ 20/ 2015 ዓ.ም በቻይና ሼንዘን ከተማ በተካሄደው 7ኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር 9 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።
የትምህርት ሚኒስቴር ለውድድሩ ተሳታፊ ተማሪዎቹ መልካም ውጤትን ይመኛል።