News Detail
Jun 01, 2024
2.2K views
የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎቹን በት/ቤታቸው ለማስፈተን ምን ማሟላት አለባቸው?
በዚህ አመት በኦንላይን የተዘጋጅውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ አገር አቀፍ ፈተናን ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ለማስፈተን ፍላጎት ያለው ማንኛዉም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የተደራጀ የኮምፒዉተር ላብራቶሪ ሊኖረው ግድ ይለዋል። ይሄውም:
1. ዴስክቶፕ ወይም ላፕቶፕ ኮምፒዉተሮች
2. የዉስጥ ኔትዎርክ ያለዉ (የገመድ) ኔትዎርክ/Local Area Network /
3. የኢንተርኔት መስመር ከበቂ ባንድዊድዝ ጋር እንደ የመፈተኛ ኮምፒዉተር ብዛት
4. የባክ አፕ ፓዎር (ጄኔሬተር)
ጋር አሟልተው መገኘትና ለትምህርት ቢሮዎች በማሳወቅ በቢሮዎች በኩል መሟላቱ ሲረጋግጥ የፈተና ማእከል በመሆን ተማሪዎቹን ማስፈተን እንደሚችሉ እያሳውቅን ለፈተና የሚዘጋጁት ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒዉተሮች ማሟላት ያለበቸዉ ትንሹ ስፔስፊኬሽን እንደሚከተለው ቀርቧል።
1. RAM --------------- 4GB or higher
2. Storage --------------250GB or higher
3. Processor Speed -------- 2.5GHZ or higher
4. Processors ---------- Intel Core i3 or higher
5. OS --------------- Windows 10
6. Browsers ---------------Safe Exam Browser and other
7. Accessories ---------- Keyboards and Mouse for desktop computers.
ትምህርት ሚኒስቴር
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024