News Detail

National News
Apr 11, 2024 569 views

የትምህርት ሚንስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የትምህርት ሚንስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደርን Jorge Fernando Lefebre Nicolas በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን ውይይታቸውም በኢትዮጵያና በኩባ የህክምና ትምህርት ተቋማት መካከል የተቋም ተቋም ግንኙነትን ማጠናከር፣ የምርምር ስራዎችን በጋራ መስራት፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችና የህክምና ባለሙያዎች ልወውጥ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነበር።
ክቡር ሚኒስትሩ ከክቡር አምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ውይይትም የአንጋፋው የያሬድ የሙዚቃ ት/ቤትን ለማጠናከር ከአፍሮ ኪዩባን ባህላዊ ማዕከል ጋር በጋራ በሚሰሩበት ዙሪያ ስምምነት አድርገዋል። የተቋማቱ ስምምነት የሀገራቱን የባህላዊ ሙዚቃ ልውውጥ የሚያሳድግ ሲሆን ለያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ደግሞ አለምአቀፍ የሙዚቃ ባህል ልውውጥ ለማድረግ እንዲችል እድል የሚሰጥ እንደሆነ ተገልጿል።
Recent News
Follow Us