News Detail

National News
Jul 23, 2025 100 views

ኢትዮጵያና አልጄሪያ በትምህርትና ስልጠና መስክ ያላቸውን ትብብር ሊያሳድጉ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር የሆኑትን ዶ/ር መሀመድ ካሊድን በ/ጽቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ሚንስትሩ ከአምባሰደሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ እየተለወጠ ባለው የአለም ስርዓት ውስጥ አፍሪካውያን ትብብራቸውን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባቸው የገለጹ ሲሆን በትምህርት ዘርፍ ከአልጄሪያ ጋር በትብብር ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ ከዚሁ ጋር አያይዘው ባረጉት ገለጻ በኢትዮጵያና አልጄሪያ መካል ያለውን የትምህርትና ስልጠና ትብብር ከማጠናከር ባለፈ በሀገራቱ የጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ምርምሮችን በጋራ ለመስራት ፣የመምህራንና ተማሪዎች ልውውጥ ለማድረግ ፣ የነጻ ትምህርት እድሎችን ለማመቻቸት እንዲሁም የቴክክና ሙያ ትምህርት አሰልጣኞች ስልጠና ላይ አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር ዶ/ር መሀመድ ካሊድ በበኩላቸው ኢትዮጵና አልጀሪያ በቀጠናዊና አለማቀፋዊ የገራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ትብብር ያላቸው መሆኑን የገለጹ ሲሆን ይህን ዘርፈ ብዙ ትብብር ማስፋትና ማሳደግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
አምባሳደሩ በማያያዝ እንደገለጹት የአልጄሪያ መንግስት በኢትዮያ በኩል የሚቀርብለትን የትብብር ፍላጎት መሰረት በማድረግ ስምምነት የመፈራረምና አብሮ የመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
Recent News
Follow Us