News Detail

National News
Feb 21, 2022 2.2K views

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የአገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ ም 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል።

የትምህርት  ሚኒስቴር አገር አቀፍ የትምርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር  አቶ ተፈራ ፈይሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሁለት ዙር የተሰጠው 2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ለአገር አቀፍ ፈተና  ከተመዘገቡት 617,991 ተማሪዎች መካከል 599,003 (96.9%) ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡ 

በመጀመሪያ ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት በመታየቱ ምክንያት የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል መወሰኑን ጠቁመዋል።

አቶ ተፈራ ፈይሳ አክለውም ሁሉም ተማሪዎች የግልም ሆነ የመንግስት የከፍተኛ ትምህርትን ለመከታተል ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ማምጣት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል።


ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ተወስኖ  ወደፊት ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡  

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot - 
4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡ አውንታዊ ድጋፍ ለሚሹ አመልካቾች፡- student.ethernet.edu.et በመግባት ማመልከት ይችላሉ።

Recent News
Follow Us