News Detail

National News
Feb 11, 2022 1.7K views

ለወደሙ ትምህርት ተቋማት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

እጅጋየሁ ሞል የተባሉ በጀርመን አገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እየተደረገ ባለው የሀብት ማሰባሰብ መርሀ ግብር ግማሽ ሚሊዬን ብር ድጋፍ አደርገዋል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በጀርመን አገር ከሚያውቋቸው ወገኖች አሰባስበው ካስረከቡት ግማሽ ሚሊዮን ብር በተጨማሪ ለተፈናቀሉ ተማሪዎች እንዲውል 2016  ደብተሮችንና 300 እስክሪብቶዎችንም ለግሰዋል።

ወ/ሮ እጅጋየሁ ድጋፍ ያደረጉት የትምህርት ሚኒስቴር ባቀረበው ጥሪ መሰረት ለወደሙ ትምህርት ቤቶችና ለተፈናቀሉ ተማሪዎች ጥቅም እንዲውል በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የእቅድ በጀትና ሀብት ማፈላለግ ጀነራል ዳይሬክተር  አቶ ኤሊያስ ግርማ ለተደረገው ድጋፍ  ምስጋና አቅርበው ድጋፉን ተረክበዋል።

ድጋፉ በቀጥታ ለወደሙ ትምህርት ቤቶችና ለተጠቃሚ ተማሪዎች እንደሚውልም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ''' ኑ የፈረሰውን የትውልድ ማፍሪያ ተቋም መልሰን እንገንባ '' በሚል መሪ ቃል ለወደሙ ትምህርት ቤቶች ማሰሪያ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ከዚህም መካከል 9222 አጭር የፁሁፍ መልዕክት አንዱ ነው።

በሰሜኑ ክፍል በነበረው ጦርነት ከ 4ሺ በላይ የትምህርት ተቋማት በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ይታወሳል።

Recent News
Follow Us