News Detail
ለወደሙ ትምህርት ተቋማት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በጀርመን አገር ከሚያውቋቸው ወገኖች አሰባስበው ካስረከቡት ግማሽ ሚሊዮን ብር በተጨማሪ ለተፈናቀሉ ተማሪዎች እንዲውል 2016 ደብተሮችንና 300 እስክሪብቶዎችንም ለግሰዋል።
ወ/ሮ እጅጋየሁ ድጋፍ ያደረጉት የትምህርት ሚኒስቴር ባቀረበው ጥሪ መሰረት ለወደሙ ትምህርት ቤቶችና ለተፈናቀሉ ተማሪዎች ጥቅም እንዲውል በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የእቅድ በጀትና ሀብት ማፈላለግ ጀነራል ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ግርማ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ድጋፉን ተረክበዋል።
ድጋፉ በቀጥታ ለወደሙ ትምህርት ቤቶችና ለተጠቃሚ ተማሪዎች እንደሚውልም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ''' ኑ የፈረሰውን የትውልድ ማፍሪያ ተቋም መልሰን እንገንባ '' በሚል መሪ ቃል ለወደሙ ትምህርት ቤቶች ማሰሪያ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ከዚህም መካከል 9222 አጭር የፁሁፍ መልዕክት አንዱ ነው።
በሰሜኑ ክፍል በነበረው ጦርነት ከ 4ሺ በላይ የትምህርት ተቋማት በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ይታወሳል።
Recent News
የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
Feb 27, 2026
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
Feb 13, 2026