News Detail
የትምህርት ሚኒስቴር የኦንላይን መማሪያ ስርዓትን እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎቶችን መስጠት ጀመረ
የኢለርኒንግ እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎቶቱ መደበኛና አጋዥ መጽሃፍት፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ትምህርት ሚኒስቴር ካዘጋጃቸው እና ለተማሪዎች ይጠቅማሉ ካላቸው ከተለያዩ የውጭ ምንጮች በማካተት ይዞ ቀርቧል::
አገልግሎቱ ለተማሪዎች ግብዓቶችን በክፍል፣ በትምህርት አይነት፣ በምዕራፍ በመምረጥ ለአጠቃቀም ቀላል ሆኖ ቀርቧል፡፡
በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞችን እና ወደ ትምህርት ቤት መምጣት የማይችሉ ተማሪዎችን ችግር እንዲያቃልል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን ልዪ ተሰጥኦ ያላችውን ተማሪዎች የትምህርት ስርዓቱን ሳይገደቡ መከታተል ያስችላልም ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከሶስት ሺ በላይ የሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመማር ማስተማር ግብዓቶብን በክፍል፣ በትምህርት አይነት እና በምዕራፍ ተከፋፍሎ ወደ ሲስተሙ የመጫን ስራ ተሰርቶ ግብዓቶቹን በነፃ በኢንተርኔት እና ከኢንተርኔት ውጪ በማውረድ መጠቀም ያስችላል፡፡
በቀጣይም ለመጀመሪያ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የዚሁ አግልግሎት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ በፈጣን ሁኔታ እየተሰሩ መሆናችው ተገልጿል።
ተማሪዎችም የኢለርኒንግ እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎትን ለማግኘት የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል https://elearn.moe.gov.et
Recent News
የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
Feb 27, 2026
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
Feb 13, 2026