News Detail

National News
Oct 19, 2021 1.5K views

በትግራይ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡
በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከ ዛሬ 09/02/21014 ዓ.ም እስከ 12/ 02/2014ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡
ለመመዝገብ https://forms.gle/wYpZtTqpdQ417Bxx8 በመጠቀም የተቀመጠውን ፎርም እንዲሞሉ እና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
Recent News
Follow Us