News Detail
Oct 19, 2021
392 views
ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን በውጤታማነት ለመተግበር እየተሰራ ነው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ ከዲቪቪ ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ከፌደራልና ከክልል ትምህርት ቢሮ ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክተር ጀነራል ታምራት ይገዙ (ፒ.ኤች.ዲ) ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን በውጤታማነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ይህንን ሊተገብር የሚችል ሀይል ለማደራጀት ይህ የምክክር መድረክ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
ዳይሬክተር ጀነራሉ አክለውም የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ሥርዓትን ለማስቀጠል የሚያስችል አሰራርና ስልት ተቀይሶ ክህሎትን መሰረት ያደረገ ትምህርት ለመስጠት ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል፡፡
የዲቪቪ ኢንተርናሽናል ዋና ዳይሬክተር አቶ እሸቱ አባተ ይህ ወርክ ሾፕ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ሥርዓትን ለማስቀጠልና ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ የጎልማሶች ትምህርትን ተግባራዊ ለማድረግ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን በትምህርት ቤት ደረጃ ተግባዊ ለማድረግ በየትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህራን እዲኖሩ የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024