News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 19, 2021 332 views

የጎልማሶች ትምህርት ሥርዓት ለማስቀጠል የተቀናጀ ሰራ መሰራት አለበት ተባለ፡፡

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምርት ዘርፍ ከዲቪቪ ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ከፌድራልና ከክልሎች ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች የጎልማሶች ትምህርት ስርዓት ግንባታ መሰረቶች ላይ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ስርዓትን በወጥነት ለማሰቀጠል የሁሉንም የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት የባህርዳር የኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ረዳት ፕ/ር ሙሉጌታ አዋየሁ ገለፀዋል፡፡
ረዳት ፕ/ር ሙሉጌታ አዋየሁ የጎልማሳ ትምህርት ስርዓት ግንባታን ለማስቀጠልና ውጤታማ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎችን፣ተቋማዊ አደረጃጀቶችን፣አስተዳደራዊ ጉዳዮችን እንዲሁም የትግበራ ሂደቶችን በሚገባ ለይቶ ክፍተቶችን በመሙላት መተግባር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግና የተማረና በኢኮኖሚ የዳበረ ማህበረሰብ በሀገራችን እንዲፈጠር እንደመንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊሰራ እንደሚገባም አብራርተዋል፡፡
መምህሩ አክለውም በሀገራችን የተደራጀ የጎልማሳ ትምህርት ስርዓትን ለመዘርጋት እነዚህን ጉዳዮች በሚገባ ተረድቶ ክፍተቶችን በመሙላት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል፡፡
Recent News
Follow Us