News Detail

National News
Oct 23, 2021 286 views

የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ሥርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍን የማሻሻል ስራ እየተሰራ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት ላይ የነበሩበትን ክፍተቶች ለመለየት የሚያስችል የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩ ከዚህ በፊት ለጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት የተዘጋጀው መርሃ ስርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ በአተገባበር ረገድ ውጤታማ አልነበረም ተብሏል፡፡
ስርዓተ ትምህርቱ ከዓላማ ፣ከይዘት እና አቀራረብ ከማስተማሪያ ስነ-ዘዴዎችና ከሚጠበቀው ውጤት አንፃር በሚገባ የተቃኘ አልነበረም ሲሉ በትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘላለም አላጋው ገልፀዋል፡፡
ባለሙያው አክለውም የጎልማሳውን ነባራዊ ሁኔታ፣ የመንግስትና የጎልማሳውን ፍላጎትን መሰረት ያደረገ እና ከሳይንሱ ጋር የተጣጣመ የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት እንዲኖር የማሻሻያ እና ክለሳ ስራ እየተሰራ እንዳለ ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የነበረው ስርዓተ-ትምህርት ለ10 ዓመታት የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት በሚል ሲሰጥ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በመድረኩም የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
Recent News
Follow Us