News Detail
Nov 16, 2020
688 views
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በ 5ሚሊዬን ብር ወጪ የተሰሩ ዘመናዊ የተማሪዎች የእጅ መታጠቢዎች ለትምህርት ቤቶች ተሰራጩ፡፡
የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ከተባበሩት መንግስታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ጋር በመተባበር ከአምስት ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆኑ የእጅ መታጠቢያዎችን ለትምህርት ቤቶች አሰራጭቷል፡፡
የተመረቱት ዘመናዊ የእጅ መታጠቢያዎች ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ እጆቻቸውን በተደጋጋሚ በመታጠብ ኮቪድን ለመከላከል እንዲችሉ መሆኑ ተነግሯል፡፡
የእጅ መታጠቢያዎቹ ለ100 አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተሰራጩ ሲሆን የእጅ መታጠቢያዎቹ ሙሉ በሙሉ በዩኒሴፍ ወጪ የተሸፈነ መሆኑንም ትምህርት ቢሮው አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዩኒሴፍ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት በክልሉ ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 በመከላከል ወደ መማር ማስተማር ስራ መግባታቸው ይታወሳል።