News Detail
Nov 16, 2020
720 views
በአዊ ብሄረሰብ ዞን ከ5ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባው ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በገዛራ ቀበሌ የተገነባው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቆ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ ሆኗል።
ትምህርት ቤቱ በህብረተሰቡ ተነሳሽነት 5 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ እና ፓርትነር ኢን ኢጁኬሽን ኢትዮጵያ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር መገንባቱ ነው የተነገረው፡፡
በምረቃ ስነስርአቱ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ (ፒ እፕች ዲ) በራሳችሁ ገንዘብና ተነሳሽነት የልጆቻችሁ ቤት የሆነውን ህንፃ አጠናቃችሁ ለዚህ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ የተገነባው ተማሪዎች እንዲማሩበት በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ ሃላፊነቱን እንዲወጣ የቢሮ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ትምህርት ቤቱም ለመማር ማስተማሩ የሚያግዙ የውስጥ ቁሳቁስ የተሟላለት ሲሆን ፕሮጀክቱ በቀጣይ አምስት ዓመት የመማር ማስተማሩን ሂደት በመደገፍ ቆይታ ያደርጋል ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ ባለፉት ዓመታት በዞኑ በርካታ ትምህርት ቤቶችን ህብረተሰቡን በማስተባበር መስራቱ ይታወሳል፡፡