News Detail
Nov 03, 2020
660 views
ከክፍያ ጋር በተያያዘ እገዳ የተላለፈበት ትምህርት ቤት በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንዲከፈት ተወሰነ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ባለመተግበሩ እና ወላጆች በተደጋጋሚ ለትምህርት ሚኒስቴር ባቀረቡት ቅሬታ እገዳ የተላለፈበት ትምህርት ቤት በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እገዳው ተነስቶለታል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው የሱፐርቪዝን ስራ ትምህርት ቤቱ አስፈላጊውን ማስተካካያ ማድረጉ እና ከወላጅ ኮሚቴዎች ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰ መሆኑንን ቢያረጋግጥም
ትምህርት ቤቱ ትምህርት ሚኒስቴር የጣለበትን እገዳ ሳያነሳ እና ሳያሳውቅ ትምህርት በመጀመሩ ትምህርት ቤቱ በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንዲከፈት መወሰኑ ተገልጿል፡፡
በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እገዳው የተነሳለት አንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ከዛሬ ጀምሮ በመመሪያው መሰረት መደበኛ ስራውን ማከናወን እንደሚችልም ተነግሯል፡፡
ከዚህ በኋላ ትምህርት ቤቱ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣውን ማናቸውም መመሪያዎችን ተላልፎ ከተገኘ ትምህርት ቤቱን እስከ መዝጋት የሚያደርስ እርምጃ እንደሚወሰድም ትምህርት ሚኒሰቴር አስታውቋል፡፡
ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በመከተል የመማር ማስተማሩን ሄደት ማስቀጠል እንዳለባቸው ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡