News Detail
Oct 24, 2020
630 views
በዚህ አመት 5 ሚሊዬን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ይኖራቸዋል:- ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በBiometric Digital Registration በመጪው ሰኞ እንደሚጀመር አስታውቃል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ የዲጂታል መታወቂያ ትግበራ የመጀመሪያዎቹ 450ሺ ተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ እንደሚኖራቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ገለፀዋል።
በዚህ አመት ደግሞ 5 ሚሊዬን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ይኖራቸዋል ብለዋል።
የተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማድረግ አንዱ አካል ነው።